ኃይለማሪያምና ሮማን የተባለ ፋውንዴሽን ሊቋቋም ነው

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ጋር "ኃይለማርያም እና ሮማን" የተሰኘ ፋውንዴሽን ሊያቋቁሙ ነው።

ፋውንዴሽኑ ጥቃት የደረሰባቸውና ሌሎች ድጋፍ የሚፈልጉ ሕጻናትና ሴቶችን መንከባከብ ላይ አተኩሮ ይሰራል ተብሏል።

አገር አቀፍ የሴቶች ማረፊያ ማኅበርና የሴቶች ይችላሉ ማኅበር ወደ አመራርነት የመጡ ሴቶችንና ድጋፍ ያደረጉ አካላትን እውቅና ለመሥጠት የምስጋና መርኃ ግብር በአዲስ አበባ አዘጋጅተዋል።

በዚሁ ጊዜ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ከባለቤታቸው ጋር በመሆን "ኃይለማርያም እና ሮማን" የተሰኘ ፋውንዴሽን ሊቋቋም መሆኑን ጠቁመዋል።

ፋውንዴሽኑን ለማቋቋም የሚያስፈልጉ የዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቃቸውን የገለጹት ወይዘሮ ሮማን ፋውንዴሽኑ በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገባ ፍንጭ ሰጥተዋል።