ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል ሓሳብ አቀረቡ

ጠቅላይ ሚነስትር  ዶክተር አብይ አህመድ  በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለአገሪቱ  የውጭ  ምንዛሪ መጎልበትና የልማት  ሥራዎች ተገቢውን  አስተዋጽኦ ለማድረግ እንዲችሉ የሚያደርግ   ጠቃሚ  ሓሳብ በዛሬው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት  አቅርበዋል ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2011  ረቂቅ  በጀት በተመለከተ በሠጡት ማብረሪያ እንደገለጹት በተለያዩ  የዓለም ክፍሎች  የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ አገራቸው የሚልኩትን የውጭ  ምንዛሪ  በባንኮች  ብቻ  እንዲሆን በማድረግ  አስተዋጽኦቸውን ማሳደግ የሚያስችል ሓሳብ አቅርበዋል ።

በውጭ  የሚገኙ ኢትዮጵያውያን  ወደአገራቸው የሚልኩትን የውጭ  ምንዛሪ  ትረስት ፈንድ በመቋቋም እያንዳንዱ በውጪ  የሚኖር ኢትዮጵያዊ  በየቀኑ  ከሚወስደው ማኪያቱ በመቀነስ አንድ ዶላር  መዋጮ  ቢያደርግ እንኳን በዓመት  ከፍተኛ  ገንዝብ  መሰብሰብ እንደሚቻል ተናግረዋል ።

በአጠቃላይ  በመላው ዓለም  3  ሚሊዮን  የሚሆኑ  ኢትዮጵያውያን  በተለያዩ አገራት  የሚኖሩ  መሆኑን  የገለጹት  ጠቅላይ ሚንስትሩ  በውጭ  የሚኖሩ ዜጎች   በቀን አንድ ዶላር ለአገራቸው  ማዋጣት  ቢችሉ እንኳን  በአገሪቱ ለሚከናወኑ  የተለያዩ  መሠረታዊ የልማት ሥራዎችን  በፈቃደኝነት መደገፍ እንደሚችሉ  አስረድተዋል ።

ኢትዮያውያን   አገራቸውን  ባላቸው አቅም  እንዲደግፉ  ማድረግ  ከዚህ ቀደም  የነበራትን ታሪክ ለመቀየር እንደሚያስችል የጠቆሙት ለዚህም ሓሳብ በውጭ  የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያን  ሓሳቡን  ተግባራዊ ለማድረግ ቀና ትብብር  እንደሚያደርጉም  እምነታቸው መሆኑ ጠቅላይ ሚነስትር ዶክተር  አብይ  ተናግረዋል ።

በተጨማሪም  በውጭ  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሙሁራን በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በሙያቸውም   ድጋፍ የሚያደርጉበት  ሁኔታም መመቻቸት እንዳለበት   በምክር ቤቱ  ገለጻ አድርገዋል ።

የተለያዩ  አገራት  በውጭ  አገራት  የሚኖሩ  ዜጎቻቸውን  የሙያና ገንዘብ  አቅም በመጠቀምም   ተጨባጭ  ውጤት  እያስመዘገቡ መሆኑን   ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠቅሰዋል ።