የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአዲስ አበባ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገለጸ ።
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በውይይታቸው ላይ የተለያዩ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ በኤርትራ ጉብኝት ማድረጋቸውንና የሁለቱ አገራት ግንኙነት መሻሻሉን ተከትሎ ነው አንቶኒዮ ጌተሬዝ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረግ የፈለጉት ።
የኢትዮጵያ ኤርትራ አየር መንገዶችም በረራ እንዲያደርጉና በወደቦች በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ያስታወቁ ሲሆን ፥ የሁለቱ ሃገራት ህዝቦች ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዲችሉም ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም አንስተዋል።
የተመድ ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 2ኛው የጋራ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ ።