የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርም ደሳለኝ የዝምባብዌን አገራዊ ምርጫ እንዲታዘቡ ተመረጡ

ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርም ደሳለኝ በዝምባብዌ በሚካሄደው ምርጫ የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን እንዲመሩ ተመረጡ።

የዝንባብዌ መንግስት ከጥቂት ወራት በፊት ዘንድሮ የሚካሔደውን ምርጫ እንዲታዘቡ የአውሮፓና የአፍሪካ ሕህረትን ጨምሮ የመንግስታቱ ድርጅትን የልኡካን ቡድን እንዲታዘቡ ጋብዘው ነበር።

በዚህም የአፍሪካ ሕብረት ሁለት ቡድን ያለው የታዛቢዎች አካላት የአገሪቱን ምርጫ እንዲታዘብ የወሰነ ሲሆን አንዱን ቡድን የመምራት ስራ ለቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃለማርያም ደሳለኝ በሕብረቱ መመረጣቸው ተገልጿል።

ህብረቱ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ምርጫውን የሚታዘበውን የልዑካን ቡድን እንዲመሩ ያደረጉት በአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት በነበራቸው ተሳትፎ ነው።

አቶ ኃይለማርያም በዚሁ መሰረትም ከአስር ቀን በኋላ ወደ ሀረሬ እንደሚያመሩም ተጠቁሟል።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአገራታቸው ብሎም በአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የዲሞክራሲ ስርዓትን ለመገንባትና በተለያዩ አለማቀፍና አሕጉር አቀፍ መስሪያ ቤቶች ውስጥ ባደረጉት ተሳትፎ እንደተመረጡ ተጠቁሟል።

ከዚህ ውስጥም አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ሕብረት ሰላምና ፀጥታ፣ የኔፓድና የሕብረቱ ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል። (ኢዜአ)