የሃብሊ ሊቀ መንበር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ ከኃላፊነት ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ(ሃብሊ) ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ ከድርጅቱ ሊቀመንበርነት ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ አሰናበተ፡፡ 

ሊጉ ለሁለት ቀናት ባካሄደው ግምገማ ነው አቶ ሙራድ ያቀረቡትን መልቀቂያ  ማዕከላዊ ኮሚቴው በጥልቀት ከገመገመ በኋላ ተቀብሎ አሰናብቷል፡፡

በተጨማሪም በምክትል ሊቀመንበርነት ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ ያሲን ሁሴን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ውሳኔም ተቀብሏል፡፡

በዚህም መሰረት በአቶ ሙራድ አብዱልሃዲ ምትክ አቶ ኡርዲን በድሪን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል፡፡

አቶ ነቢል ማህዲን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ሊጉን እንዲመሩ በመወሰን ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቋል ሲል ፤ የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ለዋልታ  በላከው መረጃ ገልጿል ፡፡