ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ተቋም ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ ሆኖ ይሰራል- ጄነራል አደም መሃመድ

ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ተቋም ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ እና ከህዝቡ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እንደሚሰራ የተቋሙ ዳይሬክተር  ጄነራል አደም መሃመድ አስታወቁ፡፡

ጄነራል አደም በብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ከአዲሱ አመራር ጋር ትውውቅ ባደረገበት መድረክ  እንደተናገሩት ተቋሙ እንደ ከዚህ ቀደሙ በህዝብ ዘንድ የሚፈራ ሆኖ አይቀጥልም ብለዋል፡፡

የውስጥ መረጃና ደህንነት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረ መድኅን በበኩላቸው  ተቋሙ ሁሉን አቀፍና ብቃት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት ኢትዮጵያዊ ተቋም ሊሆን እደሚገባም ጠቁመዋል፡፡