የትግራይ ክልል ተወላጅ ምሁራን ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በመቀሌ ተጀመረ

የትግራይ ክልል ተወላጅ ከፍተኛ ምሁራን የተሳተፉበት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ዛሬ በመቀሌ ከተማ  የሰማእታት ሐውልት የመሰብሰቢያ አደራሽ ተጀመረ።

በኮንፈረንሱ  ” ትግራይ ከየት ወዴት”  በሚል አጀንዳ ላይ ውይይት ይካሄዳል፡፡

በተለይ የትግራይ ክልል ህዝብን ከድህነትን ለመውጣት በምርምርና ጥናት ላይ ያተኮሩ የመፍትሄ ሃሳቦችን በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ይደርግባቸዋል።

የክልሉ ተወላጅ ምሁራን ማህበር ሊቀመንበር ዶክተር ገብረ ኪዳን ገብረ ስላሴ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ወቅት እንዳሉት ኮንፍረንሱ የተሰናዳው በአጀንዳው መሠረት  ክልሉ ያሉበትን ችግሮች ለመፍታት በምርምርና ጥናት ላይ ተመስርተው ምሁራን የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማነሳሳት ነው፡፡

ለአምስት ቀናት በሚቆየው በዚሁ ኮንፈረንስ ከ1 ሺህ 300 በላይ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች፣ከትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ምሁራንና ሌሎችም አካላት እየተሳተፉ ነው።(ኢዜአ)