አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከ20 ዓመታት በኋላ በኤርትራ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

አምባሳደር ሬድዋን በአየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው  ሲያገለግሉ እንደነበር  ይታወሳል።

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኤርትራ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ   ለማጠናከር   የሚሠራ መሆኑን  አስታውቋል።