በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጋዶ ሚጢ ወረዳ ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው የፀጥታና ያለመረጋጋት ችግር ረግቦ ወደ አንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት መስፈኑን የክልሉ የፀጥታ ቢሮ አስታወቀ ።
የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ ለዋልታ ቴሌቭዥን እንደገለጹት በተያዘው ሳምንት የክልሉ የፀረ-ሽምቅ ኃይል አባል ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን ተከትሎ በሚጢ ወረዳ የሚገኙ ወጣቶች ሁከት መፍጠራቸው ይታወሳል፡፡
በወረዳው በተፈጠረው የፀጥታ ሂደት መስተጓጎልም ሁለት ሰዎች መሞታቸውንና ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን ተገልጿል ።
ሰሞኑን በአጋዶ ሚጢ ወረዳ የተከሰተውን ሁከትን ተከትሎ ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገው ተከታታይ ውይይት በወረዳው ሙሉ በሙሉ ወደ ሰላምናመረጋጋት መመለሱን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡