ኤርትራ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር የሚገኘውን ጦሯን ሙሉ ለሙሉ አስወጣች

ኢትዮጵያና ኤርትራ የደረሱበትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ኤርትራ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አካባቢ ሠፍሮ የሚገኘውን  ጦሯን  ሙሉ በሙሉ አስወጣች ፡፡

አልጀዚራ ኤርትራ ፕረስ ኤጀንሲን በዋቢነት ጠቅሶ እንደዘገበው ይህ የኤርትራ ውሳኔ ሀገራቱ እርቅ ማውረዳቸውን በተግባር የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ሁለቱ አገራት መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመጀመር  መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን በቅርቡ በአዲስ አበባ የኤርትራ ኤምባሲ ሲከፈት በአስመራም የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደሚከፈት ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የሁለቱ አገራት አየር መንገዶች በረራ እና  የስልክ አገልግሎት መጀመራቸውም አይዘነጋም፡፡

አሁን ደግሞ የኤርትራ ጦር ሰፍሮባቸው ከነበረው የኢትዮ ኤርትራ የድንበር አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ማስወጣት ለሀገራቱ ሰላም የላቀ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡