አምባሳደር ግርማ ብሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

አምባሳደር ግርማ ብሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዶክተር አብይ አህመድ አምባሳደር ግርማ ብሩን የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ በማድረግ ሾመዋቸዋል።

ከትናንት ጀምሮም አቶ መኮንን ማንያዘዋልን በመተካት የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸውን  ተገልጿል።

አምባሳደር ግርማ ከዚህ ቀደም በቀድሞው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር በመሆን ማገልገላቸው ይታወሳል።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደግሞ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል።

ከአምባሳደር ግርማ ሹመት ባለፈም የፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም ተከስተ እና የቀድሞው የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የባንኩ የቦርድ አባላት ሆነዋል።

አቶ በቃሉ ዘለቀ ደግሞ የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዥ በመሆን መሾማቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።(ኤፍቢሲ)