የይቅርታና ምህረት አዋጁ ለስድስት ወራት ያህል ሥራ ላይ እንደሚውል የጠቅላይ አቃቢ ህግ ዋና አቃቢ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ገለጹ ።
ጠቅላይ አቃቢ ህጉ በዛሬው ዕለት በሠጡት መግለጫ እንደተናገሩት ሐምሌ 13 ፤ 2010 ዓም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የይቅርታና ምህረት አዋጅ እስከ ግንቦት 30፤2010 ድረስ የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል ።
የይቅርታ የምህረት አዋጁ በመላ አገሪቱ ተግባራዊ ሲሆን አዋጁ ምን አይነት ወንደሎችን እንደሚመለከት አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ይፋ አድርገዋል ።
እንደ አቶ ብርሃኑ ገለጻ ህገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ የተሳተፉ ፤ በኃይልና በዛቻ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በማስፈራራት ህገወጥ ሥራ የሠሩና ያሠሩ፣ በኢትዮጵያውያን ዜጎችና ተቋማት ላይ ጥቃት የፈጸሙ ፣ የአገሪቱን ሉዓላዊነት በመድፈር የተሳረፉና የመከላከያ ሠራዊት አባላት እንዲኮበልሉ በማድረግ ወንጀል በምህረት አዋጁ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል ።
የወንጀል ድርጊት ፈጽመው የሰው ህይወት ያጠፉና በሙስና ወንጀል ጉዳያቸው እየታየ ያለና የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ግን በምህረት አዋጁ እንደማያካትታቸው ዋና አቃቢ ህጉ በመግለጫቸው አመልክተዋል ።
የምህረት አዋጁ ዋና ዓላማ በአገራዊ ለውጡን ለማፋጠን ፣ የዴሞክራሲውን ለማሳደግና የፖለቲካዊ ምህዳሩን ለማስፋት እንዲሁም የቀጣይ የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት ለማጠናከር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ዋና አቃቢህጉ ገልጸዋል ።
መንግሥትያወጀውየይቅርታና ምህረት አዋጅበወንጀል የተከሰሱ ፣ ምርመራ እየተደረገባቸው ያሉትና የተፈረደባቸውን ወንጀለኞች የሚያካትት መሆኑ ተገልጿል ።