ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋ የስራ ጉብኝት  ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አምርተዋል፡፡

በቅርቡ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አልጋ ወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አልናህያ የሚመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ የስራ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ሁለቱ ሃገራት የተለያዩ የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት ስምምነት መፈራረማቸውም ይታወሳል፡፡