አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 5 ዙር 3 ዓመት የስራ ዘመን 7 መደበኛ ጉባዔው አቶ ሚሊዮን ማቲዮስን የክልሉ ርእሰ መስተደሳድር አደርጎ ሾማል።

አቶ ሚሊዮን ቃለ መሃላ በመፈፀም ቀደም ሲል ክልሉን በርዕሰ መስተዳደርነት ሲያገለግሉ ከነበሩት አቶ ደሴ ዳልኬ ሃላፊነቱን ተረክበዋል።

አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ በቅርቡ ክልሉን የሚያስተዳድረው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን/ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመራጠቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም ደኢህዴን አቶ ኤልያስ ሽኩርን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስትዳድርና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም አቶ ወንድሙ ገብሬን የጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ በማድረግ ሾሟል፡፡