የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ሊካሄድ ነው

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ሰባተኛ መደበኛ ጉባኤ ከሐምሌ 25/2010ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡

ለሶስት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ ያለፈው በጀት ዓመት የአስፈፃሚ አካላት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶች ላይ በመወያየት እንደሚፀድቅ የክልሉ ምክር ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡

የክልሉን የ2011 በጀት እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል፡፡