ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በአሜሪካ ከሚገኙ አርቲስቶች ጋር ተወያዩ

የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በአሜሪካ ከሚገኙ አርቲስቶች ጋር ተወያዩ፡፡

ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በዋሽንግተን ውሏቸው በአካባቢው ከሚገኙ አርቲስቶች ጋር የተወያዩ ሲሆን በአምባሳደሮችና በዲፕሎማቶች አማካኝነት የሚካሄደው ትራዲሽናል ዲፕሎማሲ እያበቃለት መጥቷል ብለዋል፡፡

ዘመናዊ ዲፕሎማሲ በዲፕሎማቶች ብቻ ሳይሆን በዜጎችም የሚካሄድ ዲፕሎማሲ መሁኑን ገልጸዋል፡፡

ካገኟቸው አርቲስቶች መካካል አርቲስት አለምፀሃይ ወዳጆ እና አርቲስት መስፍን በቀለ የሚገኙ ሲሆን የመንግስትን ለውጥ የማምጣት ጥረት እንደሚያደንቁ እና እንደሚደግፉም ተናግረዋል፡፡ (ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር)