የኢትዮ-ኤርትራን ግንኙነት አስመልክቶ በመቀሌ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው

በኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች መካከል የተጀመረውን ሰላም በመደገፍ  የመቀሌ ከተማና አከባቢው ህዝብ  ሰላማዊ ሰልፍ እያካሔደ ነው።

በርካታ ቁጥር ያለው  የመቀሌ ከተማና አከባቢ ነዋሪ ወደ ድጋፍ ሰልፉ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ በአራት አቅጣጫዎች እየተመሙ ነው።

ነዋሪዎቹ የኢትዮጵያና የትግራይ ክልል ባንዴራዎችና የህወሓት አርማን አንግበው ሰልፉ ወደ ሚካሄድበት የትግራይ ክልል ስታዲዮም የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ በመግባት ላይ ናቸው።

ሰልፈኞቹ ከሚያሰሟቸው መፈክሮች መካከልም “ሁሉም ዓይነት ብሄር ተኮር ጥቃት ይቁም፣ በኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች መካከል የተፈጠረው ሰላም ዘላቂነት እንዲኖረው በቁርጠኝነት እንሰራለን፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱና የህግ ልእልና ይከበር የሚሉት ይገኙበታል።

በሰላማዊ ሰልፈፉ ከ150 ሺህ በላይ ህዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። (ኢዜአ)