በባሌ ጎባ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት በእርቀ ሰላም ተጠናቀቀ

አሳሳቾች በፈጠሩት ችግር ሰሞኑን በባሌ ጎባ ከተማ የነበረው ግጭት እርቀ ሰላም በማውረድ ተጠናቋል፡፡

በእርቀ ሰላሙ ላይ የሃይማኖት አባቶች እንዳሉት ሰላም፣ ፍቅር እና ይቅር መባባል ለሁሉም ጥሩ መሆኑን  በእርቁ ወቅት ገልጸዋል ፡፡

በኃይማኖት ሽፋን ለዘመናት አብሮ ተዋዶና በአንድነት የኖረውን ህዝብ ለመለያያት የሚጥሩ አካላት ሥርዓት በሚያሲዝ  የህዝቡን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የጎባ ከተማ ነዋሪዎችም የአካባቢው ህዝብ በኃይማኖት ልዩነት ምክንያት ለችግር ተጋልጧል  ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ የተሳሳተና ከእውነት የራቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አዳነች ሀቤቤ የባሌ ህዝብ ላቀረበው የእርቀ ሰላም ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽና ቀና ትብብርም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።(ኢዜአ)