ኢንተርፕራይዙ ከ15ሺህ በላይ ችግኞችን በአዲስ አዳማ መንገድ ዙሪያ መትከሉን አስታወቀ

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራዝ በራሱ ያዘጋጃቸውን ከአስራ አምስት ሺህ በላይ  ችግኞች በአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ አካፋይ እና በዙሪያ መትከሉን አስታውቋል፡፡

ኢንተርፕራዝ ከዚህ በፊት ከተለያዩ ሥፍራዎች ያስመጣቸው የነበሩትን  ችግኞች በራሱ የችግኝ  ማፍያ መተካቱ  የአከባቢ ጥበቃ ስራውን ቀላል እንዳደረገለት ገልጿል፡፡

ይህም ከሰባ ላላነሱ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል እንዲፈጠር ማስቻሉን የኢንተርፕራዙ የህዝብ ግንኙነት እና ማርኬቲንግ አስተባበሪ ወይዘሮ ዘሀራ መሐመድ ተናግረዋል፡፡

የመንገዱ ተጠቃሚዎች አግባብ ባልሆነ ቦታ ቆሻሻ እየጣሉ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ዘሀራ ድርጊቱ የአከባቢ ጥበቃ ስራውን እያስተጓጎለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ደምበኞች ለቆሻሻ ማስቀመጫ በተዘጋጁ ቦታዎችን  ብቻ ቆሻሻ እንዲጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅቱ ክረምት በመሆኑ አሽከርካሪዎች ቆሻሻ በተገቢው ስፍራ እንዲጣል ከማድረግ በተጨማሪ የተሳፈሪዎች ደህንነት ለመጠበቅ የፍጥነት ወሰን ጠብቅው እንዲያሽከረክሩ የኢንተርፕራይዙ የህዝብ ግንኙነት እና ማርኬቲንግ አስተባበሪያ ጥሪ አቅርበዋል ።