በማህበራዊ ተሰስር ገጾች ላይ የተሠራጨው የተሳሳተ መረጃ የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን ግንኙነት አያበላሽም

በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በተሠራጨው የተሳሳተ መረጃ የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ግንኙነት እንደማይበላሽ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ “የመደመር ጉዞ” የአሜሪካ ቆይታ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሠጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአሜሪካ ቆይታቸው በዚያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች “እስልምናን ጥላለች” ብለዋል  በሚል የወጡት ዘገባዎች ፍፁም ከእውነት የራቁ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመድረኩ ላይ ያልተናገሩት መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በመንግስትም ሆነ በመሪዎች ደረጃ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸውም አቶ መለስ አስታውቀዋል።

በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የሚበላሽ አይደለም፤ ምንም የተለወጠ ነገር የለምም ነው ያሉት።