በድሬዳዋ ከተማ በተፈጠረ ሁከት የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ

በድሬደዋ ከተማ በተፈጠረው ሁከት የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የሁከቱ ምክንያት እያጣራሁ ነው ያለው ፖሊስ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል ብሏል፡፡

ማምሻውን ከተማዋ መረጋጋቷንም የኮሚሽኑ የህዝብ ግኙነት ዲቭዥን ኃላፊ ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ ለዋልታ ቴሌብዥን ተናግረዋል፡፡