ምርጫ ቦርድ ኢዴፓን በህገ-ወጥ መንገድ እያፈረሰ መሆኑን የፓርቲው አባላት ገለጹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኢዴፓን በህገ-ወጥ  መንገድ ያፈረሰ መሆኑን የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያውያን  ዴሞክራሲያውያን ፓርቲ ( ኤዴፓ) ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ በፓርቲው በጽህፈት ቤቱ ሠጥቷል፡፡

አቶ ልደቱ አያሌውና አቶ አዳነ ታደሰ በሠጡት መግለጫ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አሟሉ ያለንን መስፈርቶች ሁሉ ብናሟላም ፓርቲውን ከፍርድ ቤት ጋር በመሆን ለዶክተር ጫኔ ከበደ እንዲተላለፍ  አድርጓል ብለዋል፡፡

በዶክተር ጫኔ ከበደ የሚመራው የፓርቲው ቡድን በበኩሉ ፓርቲው በፍርድ ቤትና በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና ማግኘቱን በመግለጽ ላይ ይገኛል ፡፡

እንደ ዶክተር ጫኔ መገለጻም ፓርቲው ውስጥ ያሉ አመራሮችም ሆነ አባሎች ከፓርቲው ሊወጡ ይችላሉ ነገር ግን ፓርቲው ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የፓርቲውን የሥራ አስፈጻሚ አባልና የጥናትና ምርምር ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ በበኩላቸው በፓርቲው  ደንብና አሠራር  መሠረት  ማህተምና ቼክ የሚይዘው የፓርቲው ዋና ጸሓፊ ሲሆን  በቦርዱና በፍርድ ቤቱ  ትዕዛዝ ግን  እንዲነጠቁ ተደርጓል ብለዋል ።

የኢዴፓ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው ደግሞ ፓርቲው መፍረስ እንኳን ካለበት 25 አባላት ያሉትን የምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ምርጫ ቦርድ በተገኘበት  መፈጸም እንዳልበት አስረድተዋል ።

ብሔራዊ  ምርጫ  ቦርድም  በህገ ወጥ መልኩ  በፓርቲው  የውስጥ አሠራርና ደንብ ጣልቃ  እየገባ መሆኑንም አቶ ልደቱ ጠቁመዋል ።