የሶማሌ ክልልን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ እየተሰራ ነው—ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ

ክልልን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ብሎ እንደ አንድ ዛፍ አንድ ቅጠል የሚገነጠል አለመሆኑንም ተናግረዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ አምርተው ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዩስን ጎብኝተዋቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በሶማሌ ክልል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት ከረጅም ጊዜ ምክክርና ውይይት በኋላ አሁን መስመር እየያዘ መምጣቱን ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

“ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንዳልነው ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ብሎ እንደ አንድ ዛፍ አንድ ቅጠል የሚገነጠል አይደለም፤ እንዲሁ በዋዛ እንበተናለን ብሎ መጠበቅ ከንቱ ህልም ነው”ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም  ህዝቡ ተረጋግቶ የእለት ከዕለት ህይወቱን እንዲመራ አሳስበዋል፡፡ (ኢዜአ)