የሱዳንና ኢትዮጵያ መከላከያ በድንበር አከባቢ በጋራ በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ተስማሙ

የሱዳንና ኢትዮጵያ መከላከያ በድንበር አከባቢ በጋራ በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ሰምምነት ተፈራረሙ፡፡

በተለያዩ ጊዜያት በጋራ ለመስራት ስምምነት ሲፈራረሙ የቆዩት የምስራቅ አፍሪካ ጎረቤታሞች ሀገራት ያሁኑ የተጠናከረ ስራ ለማከናወን የሚያስችላቸው መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የሱዳንና ኢትዮጵያ መከላለከያ ሃይሎች በትላንትናው እለት ባደረጉት ስምምነት ሁለቱም የመከላከያ ወታደሮቻቸውን ከድንበር አካባቢ ለማስወጣትና በጋራ በሚቋቋም ሀይል ሽብርተኝነትንና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስቀረት ጠንካራ ፀጥታ ለማስፈን ተስማምተዋል፡፡

ከአዲስአበባ ጋር መልካም የተባለለት ወዳጅነት ያላት ካርቱም በድንበር አካባቢ በሚደረግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወደ ግብፅና ሊቢያ ለመሻገር በሚደረግ ጥረት አልፎ አልፎ ውጥረቶች ሲሰፍኑ ይስተዋላል፡፡

በሌላ በኩል  በድንበር አካባቢ በሚኖሩ አርሶ አደሮች መካከል በእርሻ መሬት ዙሪያ ግጭት የሚከሰትበት አጋጣሚ በርካታ መሆኑም ይጠቀሳል፡፡

የሁለቱ ሀገራት የመንግስት ሀላፊዎች በካርቱም ካደረጉት ስምምነት አስቀድሞ ወደ ተግባር ለመግባት በሚረዳ ፍኖተ ካርታ በኤክስፐርቶች ተመክሮበታል፡፡

በድንበር አካባቢ የሚገኙ ወታደሮቻቸውን ለማስወጣትና በቀጣይ ወር የጋራ ሀይሉን የሚያሰማሩበት ነጥብ ከስምምነት ነጥቦቹ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ውሳኔው በሚቋቋመው ኮሚሽን አማካይነትም ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ ከወዲሁ ታምኖበታል፡፡

በዘገባው መሰረት የሁለቱ ሀገራት የድንበር ማካለል ተግባር ባፋጣኝ እንዲተገበር ጥያቄ ቀርቧል፡፡ በግጭት ምክኒያት የተወረሱ ንብረቶችም ለየባለቤቶቻቸው መመለስ የሚችሉበት  አማራጭ እንዲታሰብበት ጥሪ ቀርቧል፡፡

ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል መሰተዳድርና በሱዳን በኩል በድንበር አካባቢ ያለውን ግጭት ለማስቀረት ስምምነት መደረጉ ይታወሳል፡፡

ካሁኑ ስምምነት ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን የሰጡት የሱዳኑ ጄኔራል ከማል አብዱልማሩፍ የሀገራቱ መከላከያ ሰራዊት ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተው በቀጣይም በከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው የሚመራ ቴክኒካዊ ቡድን የሚስተዋሉቱን ችግሮች ለማስቀረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል ተሳትፎ ያደረጉት ኢታማጆር ሹም ሳረ መኮንን ሱዳንና ኢትዮጵያ የጋራ ድንበሮቻቸውን በትብብር ሲያስጠብቁ መቆየታቸውን አንስተው ባሁኑም በድንበር አካባቢ የሚከሰቱ ግጭቶች መፍትሄ አንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡

ኢታማጆር ሹም ሳረ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኩል መሾማቸውን አስታውሶ የዘገበው ሱዳን ትሪቡን ነው፡፡