የቬትናም ፕሬዝዳንት ለጉብኝት ነገ ኢትዮጵያ ይገባሉ

የቬትናም ፕሬዝዳንት ትራን ዳይ ኩአንግ ነገ ነሐሴ 17፣ 2010 ዓ.ም. ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከነገ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 23 ድረስ በሚኖራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ ከፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እና በግብፅ ከፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ጋር እንደሚገናኙ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያና ቬትናም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጋቢት 1968 ዓ.ም. እንደተጀመረ ይታወሳል፡፡