የቬትናሙ ፕሬዚዳንት ትራን ዳይ ኩአንግ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

የቬትናም ፕሬዚዳንት ትራን ዳይ ኩአንግ የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ።

ፕሬዚዳንቱ ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራን ዳይ ኩአንግ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እና ጠቅላይ ሚንስትር ዶክር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር የሚያጠናክሩ ስምምነቶችም መሪዎቹ በሚገኙበት እንደሚፈረምም የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ኢትዮጵያና ቬትናም የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1976 መሆኑን መረጃዎች ያመለከታሉ። (ኤፍቢሲ)