ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በያዝነው ወር መጨረሻ በቻይና ጉብኝት ያደርጋሉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በያዝነው ወር መጨረሻ በቻይና ጉብኝት ያደርጋሉ።

በቆይታቸውም ከፈረንጆቹ መስከረም 3 እስከ 4 ድረስ በቤጂንግ በሚካሄደው በቻይና አፍሪካ ፎረም ላይ እንደሚሳተፉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።

ከፎረሙ ጎን ለጎንም ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪ ኪያንግ ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

እንደ ፅህፈት ቤት ሀላፊው ገለፃ ቻይና ቀዳሚዋ የኢትዮጵያ የንግድ አጋር እና የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ምንጭ ናት።(ኤፍቢሲ)