የቀድሞ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ ኡመር መሐመድ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ ኡመር መሐመድ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ግለሰቡ አዲስ አበባ አትላስ ከሚገኛው መኖሪያ ቤታቸው ነው ዛሬ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

እንደ ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለጻ አቶ አብዲ በሕግ ጥላ ስር እንዲውሉ ካደረጋቸው የወንጀል ተግባራት መካከል የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የብሔር ግጭት፣ በሃይማኖት መካከል ግጭት እንዲፈጠር ማድረግ የሚሉት ተጠቅሰዋል፡፡

ፖሊስ እሳቸውን ጨምሮ በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉ ሌሎች አካላትን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነም ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው እለት ባካሄደው አስቸኳይ የአቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወሳል።

እነዚህ ስድስት የስራ ኃላፊዎች

1. የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግና ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲጀማል ቀሎንቢ

2. የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ራህማ መሀሙድ

3. የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብራሂም መሀድ

4. የውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴቅ አብዱላሂ

5. የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም መሀሙድ ሙባሪክ እና

6.የኢሶህዴፓ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ኡመር አብዲ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት ያነሳው በክልሉ ተፈጥሮ ከነበረው ሁከት ጋር በተያያዘ ወንጀል በመጠርጠራቸው መሆኑንም ተገልጿል።

/ኢቢሲ/