የፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች የመልሶ መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ተቋቋመ

ከውጭ የተመለሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ተቋቋመ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ እንደገለጹት መንግስት በውጭ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ስምምንት መድረሱን ገልጸው፤ ስምምነቱም ነፍጥ አንግበው የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን፣ ከህብረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉብትንና ዘላቂ ኑሮ የሚመሩበትን ሂደት ይጨምራል።

ይህንን በአግባቡ ለመፈጸም በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ውስጥ የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት መቋቋሙን ይፋ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቶ ተስፋዬ ይግዙን የፕሮጀክቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አድርገው መሾማቸውንም አቶ ፍፁም አስታውቀዋል።

የኢፌዴሪ መንግስት በውጭ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ስምምንት መድረሱን ተከትሎ በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸው ይታወሳል።(ኤፍቢሲ)