ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቻይና- አፍሪካ ትብብር ፎረም ለመሳተፍ ወደ ቻይና አቀኑ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቻይና- አፍሪካ ትብብር ፎረም የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቻይና አቅንተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቻይና ቆይታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ ጋር በሀገራቱ መካከል ስላለው ግንኙነት ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።

በየ3 አመቱ በመሪዎች ደረጃ በሚካሄደው ጉባኤ፥ የአፍሪካ ሀገራት ከቻይና ጋር ባላቸው የምጣኔ ሃብት፣ የመሰረተ ልማት እና የማህበራዊ ዘርፎች ላይ ምክክር ያደርጋሉ።

በጉባኤው 10 የትብብር መስኮች የያዘውን የቤጂንግ ድንጋጌ በተመለከተና ለፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያነት በወጣው የድርጊት መርሃ ግብር አፈጻጸም ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ ፎረም በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ለመሳተፍ ወደ ቤጅንግ አቅንተዋል።(ኤፍቢሲ)