ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንት አልበሽር ጋር የተወያዩት በቤጂንግ እየተካሄደ ካለው የቻይና አፍሪካ ፎረም ጎን ለጎን ነው።

መሪዎቹ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በሌሎች የትብብር መስኮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

የሁለቱን ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገርም መሪዎቹ በውይይታቸው ላይ ከስምምነት ደርሰዋል።

ለቻይና አፍሪካ ፎረም ቤጂንግ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የቻይናውን ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያይተዋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)