በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በይፋ ተከፈተ

በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ በይፋ ተከፍቶ ስራ ጀመረ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ኤምባሲውን መርቀው ከፍተዋል።

ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተዘግቶ የቆየው በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ስራውን ዳግም በይፋ ጀምሯል።

በአየርላንድ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር የነበሩት አቶ ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል።

ባለፈው ሃምሌ ኤርትራ በኢትዮጵያ የሚገኘው ኤምባሲዋን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መክፈቷ ይታወሳል።