የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከዛሬ ጀምሮ ስብሰባውን ያደርጋል

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከጳጉሜ ሦስት /2010/ ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰበሰብ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት የሕዝብና ውጪ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሳዳት ነሻ አስታውቀዋል።

ስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴው ከሁለት ሳምንት በፊት አካሂዶት በነበረው መደበኛ ስብሰባ ወቅት ከተወያየባቸው አጀንዳዎች በተጨማሪ መታየት ሲኖርባቸው በጊዜ እጥረት ምክንያት ባልተዳሰሱ ድርጅታዊና ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።

በተጨማሪም በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ በሚቀርበው የድርጅቱ ሪፖርት ላይ የሚወያይ ሲሆን አጠቃላይ የጉባኤ ዝግጅቱ ያለበትን ሁኔታም በመገምገም የቀሪ ስራዎች አፈፃፀም አቅጣጫን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።