የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል

የኢህአዴግ ምክር ቤት ከመስከረም 4  2011 ዓመተ ምህረት ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ባለፈው ሳምንት በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተገመገሙና ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ የተወሰኑ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል።

ከመስከረም አጋማሽ በኃላ በሚካሄደው 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የሚቀርብ ሪፖርት ላይም ምክር ቤቱ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በወቅታዊ ድርጅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል፡፡ (ኤፍ.ቢ.ሲ)