የምስራቅ አፍሪካ አገራት የሰላም ትብብር የአገራቱን ዜጎች የሰቆቃ ህይወት መቀየር የሚችል ነው

የምስራቅ አፍሪካ  አገራት  እያደረጉ ያሉት  የሰላም  ትብብር  የተለያዩ የአገራት  ዜጎችን ህይወት  ለመቀየር  የሚችል  ነው።

የምስራቅ አፍሪካ  በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሓፊ አምባሳደር መሃቡብ ማህሊም ለዋልታ  እንደገለጹት  የምስራቅ  አፍሪካ  ግጭትና ጦርነት ከሚያመጣው  ኪሣራ በዘላቂ ሰላም የሚገኘው ጥቅምን ለማሳደግ መሪዎች የሚያደርጉትን ትብብር  እጅግ ጠቃሚ መሆኑን  ተናግረዋል  ።

በተለይም የኢጋድ ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአመራር  ብቃታቸውን በመጠቀም  የአገራቱን የዲፕሎማሲ ግንኙነት  ለማሻሻል  የሚያደርጉትን ጥረት  የሚያስደንቅ መሆኑን  አምባሳደር መሃቡብ ጠቁመዋል ።

ሰላምና ልማት  ተነጣጥለው  የሚታዩ አይደለም  ያሉት  አምባሳደሩ በምስራቅ አፍሪካ ወጣቶች  የሥራ  እድል  እንዲፈጠርላቸው  በትምህርትና በማህበራዊ ልማቶች በአካባቢው  ለማከናወን  የቀጣናው አገራት  የእርስ በእርስ መተማመን መጠናከር እንዳለበት ጠይቀዋል ።

የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች  የሰላምና  የልማት ፍላጎትን ይበልጥ  በማጎልበት አሁን በጀመሩት  በልኩ  ለተሻለ  የኢኮኖሚ  ዕድገት እንዲተጉም  አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል ።