የአፍሪካ ህብረት አሠራርና መዋቅር እንዲሻሻል ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗ ተገለጸ

የአፍሪካ ህብረት የአሰራር እና የመዋቅር የማሻሻያ ተግባራዊ እንዲሆን ኢትዮጵያ  ቁርጠኛ መሆኗን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አስታውቀዋል፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ስድስተኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ም/ቤት ስብሰባ በህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት ነው።

በስብሰባውም የህብረቱን ኮሚሽን አሰራርና መዋቅር ለማሻሻል ከዚህ ቀደም በአባል ሀገራት መካከል በተደረሰው መግባባት መስረት የቀረቡ የማሻሻያ አማራጭ ሃሳቦች ላይ ውይይት  ተካሄዷል።(ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት)