የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ጀመረ

የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን መጀመሩን አስታወቀ፡፡

እንደ ጽሕፈት ቤቱ መግለጫ ስብሰባው ባለፈው ሳምንት በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተገመገሙና ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ የተወሰኑ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል። ከመስከረም አጋማሽ በኋላ ለሚካሄደው 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በሚቀርበው ሪፖርት ላይም ይወያያል፡፡

በተጨማሪም በወቅታዊ ድርጅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡