በአዲስ አበባ በቡራዩ ፣ በከታና ሌሎች አካባቢዎች ላይ ሰሞኑን በዜጎች ላይ የደረሰውን የግድያ አደጋ በመቃወም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰለፍ አድርገዋል ።
ለታቃውሞ የወጡት የዘረኝነት ይቁም ፣ ፍትህ በቡራዩ ፣ ከታና ሌሎች አካባቢዎች በግፍ የተገደሉ ወንድሞችንና እህቶችን ፣ ፖሊስና መንግሥት እየደረሱልን አይደለም በሚል መካሄዱን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል ።
ሰላማዊ ሰለፍ አድራጊዎቹ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በቤተ-መንግሥትና ሌሎች አካባቢዎች በመዞር ጭምር ተቃውሞ እያሰሙ ፍትህ እንዲሠጣቸው እየጠየቁ ይገኛሉ ።
አደጋውን ማድረስ እጃቸው አለበት የተባሉት አካላትን መንግሥት በማጣራት እርምጃ እንዲወስድ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሠጡት መግለጫ መናገራቸው ይታወሳል ።