ኦህዴድ ለረጅም ዓመታት በድርጅቱ ሲያገለግሉ የቆዩትን አመራሮችን በዛሬው ዕለት በክብር ሸኘ ።
ኦህዴድ እያካሄደ ባለው 9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ነው የቀድሞ አመራሮች በክብር መሸኘቱን አስታውቋል ።
ድርጅቱ ወጣት አመራሮችን ወደፊት ለማምጣት ባቀደውና ሥራዎችን ማካሄድ ተከትሎ ነው ዛሬ ለነባር አመራሮቹ ሽኝቱን ማካሄዱን ይፋ ያደረገው ።
በክብር የተሸኙት የቀድሞ የኦህዴድ አመራሮች የሚከተሉት ናቸው ።
1 አቶ አባዱላ ገመዳ
2 አቶ ጌታቸው በዳኔ
3 አቶ ኩማ ደመቅሳ
4 አቶ ግርማ ብሩ
5 አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ
6 አቶ ኢተፋ ቶላ
7 አቶ ድሪባ ኩማ
8 አቶ እሸቱ ደሴ
9 ተፈሪ ጥያሮ
10 አቶ ደግፌ ቡላ
11 አቶ ሽፈራው ጃርሶ
12 አቶ አበራ ኃይሉ
13 አቶ ዳኛቸው ሽፈራው
14 ወይዘሮ ጊፍቲ አባስያ