ኦዴፓ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ምርጫ አካሄደ

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ( ኦዴፓ) በትናንትናው ምሽት  የማዕከላዊ ኮሚቴ  አባላትን ምርጫ  አካሄዷል ።

በጅማ ከተማ እየተካሄደ ባለው 9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤም የማዕከላዊ ኮሚቴ እጩ አባላትን ለመምረጥ  ጥቆማ በማካሄድ  ነው ምርጫው  የተካሄደው።

የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጥቆማው ዴሞክራሲያዊ ትግልን ማዕከል ያደረገ መሆኑንና ትናንትና ከተመረጡት  60 የማዕከላዊ ኮሚቴ  እጩ አባላት ውስጥ  55 የሚሆኑት  ለማዕከላዊ ኮሚቴ በቀጣይ  በሚስጢር  በሚሠጥ  ድምጽ የሚመረጡ መሆናቸው  ተገልጿል ።

በ9ኛው  ድርጅታዊ ጉባኤ አዴፓ  በአጠቃላይ  ቀደም ሲል ከነበረው  81 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ቁጥር  ወደ  55 ዝቅ እንዲልም ተወስኗል ።

የማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫን  ለማካሄድ  አምስት አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴም የተመረጠ ሲሆን ምርጫውን  የማስፈጸም ሥራ  በአስመራጭ ኮሚቴው አባላት የሚፈጸም መሆኑ ተገልጿል ።

እየተካሄደ ባለው በ9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ  የመጨረሻ  የማዕከላዊ  ኮሚቴ አባላትን ለመምረጥ 995  ታሳታፊዎች  ድምጽ የሠጡ  ሲሆን 55  አባላት  የተሻለ ድምጽ በማግኘት  ተመርጠዋል  ።

በቀጣይም ከተመረጡት 55 የድርጅቱ  የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ውስጥም  ዘጠኝ  የሥራ  አስፈጻሚ  አባላት  ምርጫ እንደሚካሄድ  በጉባኤው ተገልጿል ።

በአሁኑ  ወቅትም የኦዲትና ኢንስፔክሽን ቁጥጥር ኮሚቴን አባላትን ለመምረጥ ዘጠኝ እጩ አባላት ቀርበዋል ።

ለኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ( ኦዴፓ) ማዕከላዊ  ኮሚቴ አባልነት የተመረጡት የሚከተሉት ናቸው

1 ዶክተር አብይ አህመድ

 2አቶ ለማ መገርሳ

3 ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ

4  አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ

5 ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

6ኢንጂነር ታከለ ኡማ

7 አቶ ሽመልስ አብዲሳ

8 አቶ ኡመር ሁሴን

9 ወዘሮ ጠይባ ሀሰን

10 አቶ አዲሱ አረጋ

11 ዶክተር ግርመና አመንቴ

12 ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ

13 ዶክተር ሚልኬሳ ሚደጋ

14 አቶ ተሾመ አዱኛ

15 አቶ ታዬ ደንደአ

16 ዶክተር አለሙ ስሜ

17 ዶክተር ቶላ በሪሶ

18 አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል

19 አቶ ግርማ ሀይሉ

20 አቶ ወርቁ ጋቸና

21 አቶ ሻፊ ሁሴን

22 አቶ ቶሎሳ ገደፋ

23 አቶ ፍቃዱ ተሰማ

24 አቶ ብርሃኑ በቀለ

25 አቶ አወሉ አብዲ

26 አቶ ጌቱ ወዬሳ

27 አቶ ካሳሁን ጎፌ

28 አቶ መላኩ ፈንታ

29 አቶ ታረቀኝ ገለታ

30 አቶ አበራ ወርቁ

31 አቶ መኩዬ መሃመድ

32 አቶ አህመድ ቱሳ

33 አቶ አሰግድ ጌታቸው

34 አቶ ደንጌ ብሩ

35 አቶ ነመራ ቡሊ

36 አቶ አብዱልአዚዝ መሃመድ

37 አቶ ሮባ ቱርጬ

38 አቶ ጀማል ከድር

39 አቶ ከፍያለው ተፈራ

40 አቶ መስፍን አሰፋ

41 ወይዘሪት ሌሊሴ ለሚ

42 አቶ ናስር ሁሴን

43 አቶ ሞገስ ኢደኤ

44 ዶክተር ደረጄ ዱጉማ

45 ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ እና

46 ወይዘሮ ሎሚ በዶ