ኦዴፓ የፓርቲውን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር መረጠ

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ዝያካሄደ ባለው  9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የፓርቲውን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር መርጧል።

ፓርቲው በዛሬው እለት ባካሄደው ምርጫ፦

1 ዶክተር አብይ አህመድን የፓርቲው ሊቀመንበር

2 አቶ ለማ መገርሳን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።

በዚህም መሰረት በዛሬው እለት የተመረጡት ሊቀመንበሩ እና ምክትል ሊቀመንበሩ እስከ ቀጣዩ ጉባዔ ድረስ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አመራር  ሆነው እንዲቀጥሎ  ሾሟል ።

በተጨማሪም ጉባኤው የኦዴግ  ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን  በማካሄድ  ዘጠኝ  አባላትን መርጧል ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በመሆን  የተመረጡት ዘጠኝ አባላት የሚከተሉት ናቸው ።

  1. ዶክተር አብይ አህመድ
  2. አቶ ለማ መገርሳ
  3. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ
  4. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
  5. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
  6. አቶ አዲሱ አረጋ
  7. አቶ ሽመልስ አብዲሳ
  8. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
  9. ዶክተር ዓለሙ ስሜ