በክልልና በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ 11 ፓርቲዎች ባህርዳር ከተማ እየተወያዩ ነው

በአማራ ብሔራዊ ክልል እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ አስራ አንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በባህር ዳር ከተማ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በውይይቱ ላይ የብአዴን ሊቀመንበር እና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮነን እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው የተገኙ ሲሆን መድረኩ “የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና” በሚል መሪ ቃል ነው ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመሪ ቃሉ ዙሪያ ለውይይቱ መነሻ ፅሁፍ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶክተር ዳዊት መኮንን እና አቶ ኢያሱ በካፋ በመቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

በውይይቱ የሚሳተፉት 11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ብአዴን፣.መዐህድ፣ አብን፣ አገዴፓ፣ አዴሀን፣ የአማራ ህልውና ፓርቲ፣ መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ኢራፓ፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና አርበኞች ግንቦት ሰባት ናቸው::

መድረኩ የተዘጋጀው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስተባባሪነት ሲሆን ፓርቲዎቹ በክልሉ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በጋራ ጉዳዮች ላይ በጋራ በሚሰሩበት፤ በተናጠል በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ሊደረግላቸው ስለሚገባው ድጋፍ እና መሰል ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተገልጸዋል፡፡