ኢትዮጵያ ከተለያዩ አገራት ለሚመጡ ስደተኞች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች -ዶክተር ወርቅነህ

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ለሚመጡ ስደተኞች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ተናገሩ  ፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በኒዮርክ እየተካሄደ ባለው 73ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

ለዚህም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብራ እንደምትሰራ ተናግረዋል ።

ሚኒስትሩ ሀገራትና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የስደተኞችን መነሻ ችግር ለመፍታት ጥረት ማድረግ አለባቸውም ብለዋል ፡፡

የአለምአቀፉ ማህበረሰብ ስደተኞችን የሚያስጠልሉ ሀገራት የሚደርስባቸውን ጫና መጋራት እንዳለበትም ገልፀዋል ፡፡
ስደተኛ ተቀባይ ሀገራትም የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል ፡፡

የአለም ባንክ ፕሬዝዳንት ጂም ዮንግ ኪም ኢትዮጵያ ለስደተኞች የትምህርትና የስራ እድል እየሰጠች መሆኑን ያነሱ ሲሆን ምስጋናም አቅርበዋል ፡፡(ምንጭ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ነው)