የመስቀል በዓል በሰላም እንዲበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ

የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በርካታ የእምነቱ የእምነቱ ተከታዮች፣መንግስት ባለስልጣናት የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ታደሙበት የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ እና የፀጥታ ችግር እንዳይኖር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደግፌ በዲ አስታውቀዋል፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲከበር ኮሚሽኑ ከሌሎች ፀጥታ አካላት እና ከእምነቱ ተቋም ጋር በቅንጅት እሰራ መሆኑን ኮሚሽነር ደግፌ ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ህዝብ በስፋት ወደ አደባባይ በመውጣት የሚያከብራቸው ሀይማኖታዊ በዓላት ካለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን ኮሚሽነሩ አስታውሰው የዘንድሮ የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ነው የተጠቆመው፡፡

በመስቀል ደመራ በዓልም ለበዓሉ ታዳሚዎች ደህንነት ሲባል ፍተሻ የሚኖር ሲሆን ወደ ዝግጅቱ ስፍራ ምንም አይነት አዋኪ ነገሮችን ይዞ መግባት እንደማይቻልም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን ደመራ ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚተናቀቅ እና ትራፊክ መቸናነቅ እንዳይጠር ።

ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር  ወይም ኦሎምፒያ

ከመገናኛና፣በሀያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሓኒለም፣በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መታተፊያ

ከቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

ከሳሪስ፣በጎተራ፣የቀድሞ አራተገኛ ክፍለ ጦር መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ መሾለኪያ ከጦር ሀይሎች፣ልደታ ፣ፖሊስ ሆስፒታል፣ሚክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሀር ጉምሩክ አካባቢ ከቀኑ 4፤00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስኪተናቀቅ ይለፍ ለሌላቸው ተሸከሪካሪዎች መንገዶች ዝግ መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ

-ከቦሌ በመስቀል አደባባ ወደ 4ኪሎ መሄድ ለሚፈልጉ

  ቦሌ-ወሎ ሰፈር-ኦሎምፒያ ኡራኤል ካሳንቺስ አራት ኪሎ

-ከቦሌ በመስቀል አደባባይ ወደ ጦር ሀይሎች መሄድ ለሚፈልጉ

ቦሌ ወሎ ሰፈር ጎተራ ቀለበት መንገድ ቄራ ሳር ትንባሆ ሞኖፖል ሚክሲኮ አደባባይ ጦር ሀይሎች

  • ከሜክሲኮ ለገሀር በመስቀል አደባባይ ወደ 22 መገናኛ መሄድ የሚፈልጉ

 ሜክሲኮ አደባባ ሳር ቤት ብሄራዊ ትያትር ኢትዮጵያ ሆቴል ፍል ውሀ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ካሳንቺስ ኡራኤል በ22 መገናኛ

-ከሚክሲኮ በለገሀር በአዲስ አበባ ስታዲየም መሄድ ሚፈልጉ

በለገሀር መብራት በአዲሱ ቂርቆስ መንገድ ሪቼ በቅሎቤት ጎተራ የሚወስዱ አማራጭ መንገዶችን አሽከርካሪዎች እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ጥቆማ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመርን መጠቀም እንደሚችልም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም ኮሚሽኑ ለመላው እምነቱ ተከታዮች በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡