የለገጣፎ ከተማ ነዋሪዎች ለኦዴፓ ያላቸውን ድጋፍ ገለጹ

የለገጣፎ ከተማ ነዋሪዎች ለኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ በሰላማዊ ሰለፍ ገለጹ።

ነዋሪዎቹ ደርጅቱ እስከ ዛሬ ያመጣቸው ለውጦች የሚያስመሰገኑ መሆኑን ገልጸዋል ።

ኤዴፓ የተማሩና ወጣት መሪዎችን በማካተት ለቀጣይ ስራ በመዘጋጀቱ ደስተኛ በመሆናቸው ለድጋፍ መውጣታቸውን ለዋልታ ቴሌቭዠን ተናግረዋል።

የከተማዋ ከንቲባ ድርጅቱ ያስቀማጣቸውን እቅዶች ዳር ለማድረስ ርብርብ ያደረጋል ብለዋል የለገጣፎ ከተማ ነዋሪዎች።

በተለይም ኦዴፓ በአገሪቱን ሆነ በኦሮሚያ ክልል የመልካም አስተዳደርን ለማሰፈንና የሕዝቡን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ከመቼውም ጊዜ በላይ ይሠራል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።