ብአዴን ስያሜውን ወደ “አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” መቀየሩን አስታወቀ

ለረጅም ዓመታት ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በሚል ሲጠራ የነበረው ድርጅት ስውያሜውን ወደ አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) መቀየሩን አስታወቀ  ።

በባህር ዳር ከተማ እያካሄደ ባለው 12ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ነው ፓርቲው ስያሜውን መቀየሩን ያስታወቀው ።

ብአዴን ከድርጅቱ ስያሜ በተጨማሪ የአርማ ለውጥም ማድረጉንም አስታውቋል።

አዲሱ የአዴፓ አርማ መደቡ ከላይ አረንጓዴ መሃል ላይ ጎህ ሲቀድ የሚኖር ቀለም (ቢጫ) ሆኖ ከግርጌ ቀይ እንዲሆን ተደርጓል።

እንዲሁም መሃሉ ላይ የስንዴ ዘለላ እና የኢንዱስትሪ ምልክት በግራ እና በቀኝ እንዲሆን የአባይ ወንዝ እና መጽሃፍም በአርማው መሃል ላይ እንዲካተት ተወስኗል።

12ኛው የድርጅቱ ጉባዔው እየተካሄደ ሲሆን ፥ በአሁኑ ወቅትም ከፓርቲው የሚሰናበቱ አባላት እየተለዩ መሆኑ ተገልጿል እየተካሄደ ።