ደኢህዴን ወ/ሮ ሙፈሪያትን ሊቀመንበር አቶ ሚሊዮንን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ በድጋሚ መረጠ

በ10ኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ድርጅታዊ ጉባኤ ፓርቲውን በቀጣይ ሶስት ዓመታት እንዲያገለግሉት ወይዘሮ ሙፈሪያትን ካሚልን በሊቀ መንበርነት በድጋሚ መርጧል ።

ጉባዔው እንዲሁም አቶ ሚሊዮን ማቲዮስን ደግሞ በድጋሚ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር በማድረግ ድርጅታዊ ጉባዔው በድጋሚ መርጧል።

ጉባዔው በዛሬው ብሎው የድርጅቱን ሥራ አስፈጻሚ አባላትና የኢህአዴግ ሥራ  አስፈጻሚ አባላትን  በመምረጥ  ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ።