በኢትዮጵያ ለሚኖሩ 150 የኤርትራ ስደተኞች የከፍተኛ የትምህርት ዕድል እንደሚሠጥ አስተዳደሩ አስታወቀ

በኢትዮጵያ በስደት ላይ ከሚኖሩ ኤርትራውያን መካከል 150 ተማሪዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብተው የመማር ዕድል እንደሚያገኙ በኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር የሰሜን ጽህፈት ቤት የትምህርት ኦፊሰር አቶ ኤፍሬም ሀጎስ እንደገለጹት ከ180 ሺህ የሚበልጡ ኤርትራውያን ስደተኞች በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ፡፡

የአስተዳደሩ ጽህፈት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመግባት 280 ስደተኞች የመግቢያ ፈተና ወስደው ያለፉ 150 ተማሪዎች መለየታቸውን ገልጿል ፡፡

እድሉ በሁለቱ አገራት መካከል አሁን የተጀመረውን ሰላማዊ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡

እንደዚህ አይነት  እድል ለኤርትራውያን ሲሰጥ ለሰባተኛ ጊዜ ሲሆን በየዓመቱም  ከ100 ያላነሱ ተማሪዎችም የዕድሉ ተጠቃሚ ሲሆኑ ቆይተዋል፡፡(ኢዜአ)