በአዲስ አበባ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በመጠጥ ኃይል ተገፋፍቶ በፈፀመው ጥቃት የሁለት ባልደረቦቹን ህይወት አጠፋ

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በመጠጥ ሀይል ተገፋፍቶ በባልደረቦቹ ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል እንደተናገሩት፥ የፌደራል ፖሊስ አባሉ በባልደረቦቹ ላይ በፈፀመው ጥቃትም ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ህይወት አልፏል።

ፖሊስ ጥቃቱን ለማስቆም በወሰደው እርምጃም ጥቃቱን የፈፀመው የፌደራል ፖሊስ አባል ህይወቱ ማለፉን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅም በስፍራው ተስተጓጉሎ የነበረው የትራፊክ እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ሁኔታቸው መመለሳቸውን ገልፀዋል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)