የሃዋሳ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ በ11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ለታደሙ ጉባኤተኞች የእራት ግብዣ ባደረጉበት ወቅት ዶክተር አብይ አህመድ እንደተናገሩት ዶሮ ብዙ ጮሃ (አሽካክታ) አንድ ዕንቁላል ጠብ ስታደርግ ላም ግን ድምጽ ሳታሰማ ብዙ ወተት ትሳጣለች በማለት ተናግረዋል ።
የንግዱ ማህበረሰብ ባዘጋጀው በዚህ የእራት ግብዣ ወቅትም ለኢህአዴግ ሊቀመንበር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ የውጭ ዝርያ ያላት ከ40-60 ሊትር መታለብ የምትችል የሰባት ወራት ጊደር በስጦታ አበርክተዋል።
ዶክተር አብይም ዶሮ ብዙ ጮሃ (አሽካክታ) አንድ ዕንቁላል ጠብ ስታደርግ: ላም ግን ድምጽ ሳታሰማ ብዙ ወተት ትሰጣለች" ኢህአዴግም እንዲሁ ብዙ ሳያወራ ብዙ ልማት ወደማምጣት የሚሽጋገርበት ጉባኤ እንደሚሆና በስኬትም እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት በጥሩ ምሳሌ ገልጸዋል።
በእራት ግብዣው ላይ የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ለጉባኤው ስኬት ምርቃትና ጸሎት አድርገዋል።